የማይወጣ
Yemayeweta
ትራክ 5 · 4:19 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የማይወጣ አቀበት የማይናድ ተራራ
የማይወረድ ቁልቁለት ለኢየሱስ የለምና
ጌታዬ ሁሉንም ሁሉንም የሚችል ነውና
ኢየሱስ ሁሉንም ሁሉንም የሚያስችል ነውና
ቁጥር 1 · Verse 1
የማይቻለው ለኢየሱስ ተችሎ
ሳየው ሳስተውለው ነገር ሁሉ አልፎ
አገኘዋለሁ ተቃንቶና አምሮ
ያቃተኝ ለእኔ ለጌታ ትንሽ ሆኖ
አዝማች · Chorus
የማይወጣ አቀበት የማይናድ ተራራ
የማይወረድ ቁልቁለት ለኢየሱስ የለምና
ጌታዬ ሁሉንም ሁሉንም የሚችል ነውና
ኢየሱስ ሁሉንም ሁሉንም የሚያስችል ነውና
ቁጥር 2 · Verse 2
ውጥንቅጡ ፊት ለፊት ተክቦ
የማይታለፍ ዳገት አቀበት ሆኖ
ያገደኝን አፈረሰ ንዶ
ጌታ ኢየሱስ ድካሜን ተረድቶ
አዝማች · Chorus
የማይወጣ አቀበት የማይናድ ተራራ
የማይወረድ ቁልቁለት ለኢየሱስ የለምና
ጌታዬ ሁሉንም ሁሉንም የሚችል ነውና
ኢየሱስ ሁሉንም ሁሉንም የሚያስችል ነውና
ቁጥር 3 · Verse 3
ማዕበሉን ጐርፉን ስመለከት
በሀሳብ ስዋዥቅ ስንከራተት
ተራመድኩኝ መላዕክቱን አዘዘ
ድል ተደርጐ ጠላቴ ፈዘዘ
አዝማች · Chorus
የማይወጣ አቀበት የማይናድ ተራራ
የማይወረድ ቁልቁለት ለኢየሱስ የለምና
ጌታዬ ሁሉንም ሁሉንም የሚችል ነውና
ኢየሱስ ሁሉንም ሁሉንም የሚያስችል ነውና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ