Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመሰግናለሁ

Amesegnalehu

2004 · ትራክ 13 · 5:06 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የልቤ ደረሰ ያሰብኩት ተሳካ

አደራ የሰጠሁት ኢየሱስ ነው ለካ (፪x)

ዛሬማ አርፌ ተደላድያለሁ

ሥራዬ ተሰርቶ አመሰግናለሁ (፪x)

በሬን ዘግቼ የለመንኩት

ምነው ባረገው ጌታን ያልኩት

በእጥፍ ላከው ቀዶ ከሰማይ

የልቤ ደርሷል ካሰብኩት በላይ (፪x)

የልቤ ደረሰ ያሰብኩት ተሳካ

አደራ የሰጠሁት ኢየሱስ ነው ለካ (፪x)

ዛሬማ አርፌ ተደላድያለሁ

ሥራዬ ተሰርቶ አመሰግናለሁ (፪x)

የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ

መች እዘነጋለሁ እዘምረዋለሁ

የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ

መች እዘነጋለሁ አመሰግናለሁ (፪x)

የልቤ ደረሰ ያሰብኩት ተሳካ

አደራ የሰጠሁት ኢየሱስ ነው ለካ (፪x)

ዛሬማ አርፌ ተደላድያለሁ

ሥራዬ ተሰርቶ አመሰግናለሁ (፪x)

(የልቤ ደረሰ) (፫x)

አላየሁኝም ፃድቅ ሲጣል

ዘሩም ሲለምን አጥቶ እህል

ጌታ ታሪኬን እንዲህ አርጐታል

የልቤን ሃሳብ አሳክቶታል (፪x)

የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ

መች እዘነጋለሁ እዘምረዋለሁ

የጌታን ውለታ በጥዋት በማታ

መች እዘነጋለሁ አመሰግናለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ