Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የእኔን ክፉ ለማትወደው

Yenien Kefu Lematwedew

2004 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስራመድ በሞት ጐዳና

ድካሜን ከላይ አየና

ለወጠው የኔን ፍፃሜ

ላምልከው በቀረኝ ዕድሜ (፪x)

ላምልከው በቀረኝ ዕድሜ (፬x)

ምሥጋናዬ ለአንተ ነው

ዝማሬዬ ለአንተ ነው

አምልኮዬ ለአንተ ነው

የእኔን ክፉ ለማትወደው (፭x)

ስከተል የማይጠቅመውን

ሳላውቀው ክፉና ደጉን

አንተ ነህ የሰበሰብከኝ

ማረፊያ ጥላ የሆንከኝ (፭x)

ምሥጋናዬ ለአንተ ነው

ዝማሬዬ ለአንተ ነው

አምልኮዬ ለአንተ ነው

የእኔን ክፉ ለማትወደው (፭x)

ሳነባ ልቤ ሲከፋ

ስጐተት በጠላት ተስፋ

ሰው አይደል የደረሰልኝ

እጅህ ነው ከሞት ያስጣለኝ (፭x)

ምሥጋናዬ ለአንተ ነው

ዝማሬዬ ለአንተ ነው

አምልኮዬ ለአንተ ነው

የእኔን ክፉ ለማትወደው (፭x)

ዘወትር ዘወትር ዘወትር ለሥምህ ልዘምር

ሁልጊዜ ሁልጊዜ ሁልጌዜ ላምልክህ ኢየሱሴ

አምላኬ አምላኬ አምላኬ አልኖር ከአንተ ርቄ

ወዳጄ ወዳጄ ወዳጄ ላምልክህ ፈቅጄ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ