Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላኬ የኔማ ተስፋ

Amelke Yenema Tesfa

2004 · ትራክ 10 · 4:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰው አይሆንም ብለው ሰው አረገኝ ጌታ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

ደጀን የለው ብለው ሆነልኝ መከታ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

እንዳሰቡት ሳይሆን እንዳሰበልኝ ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

ገና መቼ አዩ ይሄ ጅማሬ ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

አምላኬ የኔማ ተስፋ

እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ

የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት

በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት

አንተ ነህ የኔማ ተስፋ

እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ

የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት

በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት

በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት

በአንተ ነው ሁሉን ያለፍኩት

በአንተ ነው ቀን የወጣልኝ

ጌታዬ ተመስገንልኝ (፪x)

አስታዋሽ ለሌለኝ ለተረሳሁ በሰው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

ከተፍ ብሎልኛል ፍቅሩ በተግባር ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

እንባ ያወጡ አይኖቼ በደስታ ተሞሉ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

ህመሜኮ ያመዋል ስለሆንኩ አካሉ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)

አምላኬ የኔማ ተስፋ

እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ

የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት

በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት

አንተ ነህ የኔማ ተስፋ

እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ

የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት

በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት

በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት

በአንተ ነው ሁሉን ያለፍኩት

በአንተ ነው ቀን የወጣልኝ

ጌታዬ ተመስገንልኝ (፪x)

የምስኪኑ ወዳጅ ለተከፋው ፈራጅ

ለድሃደጉ አባት ለደከመው ብርታት (፪x)

ማረፊያ ጥላዬ

መጠጊያ ከለላዬ

ኢየሱስ ጌታዬ (፪x)

ኢየሱስ ጌታዬ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ