ሲነድ ይሰማኛል
Sined Yesemagnal
2004 · ትራክ 11 · 4:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የፍቅርህ ልክ የፍቅርህ ገደብ
በዝቶብኝ እኔስ ለማሰብ
አይጠፋም ሥምህ ከአፌ
አይወጣም ፍቅርህ ከልቤ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቀስቃሽ አልፈልግም ሳመልክህ
መች በረደ ውስጤ ያ ፍቅርህ
ሲነድ ይሰማኛል በላዬ
እወድሃለሁኝ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኢየሱሴ ለኔ ምትክ የለህ
ልቤም ሌላ አይሻ አንተ እያለህ
ከፍ የምታደርግ በአንተ ጊዜ
ዙፋንህ ሥር ልስገድ ሁልጊዜ
ተባረካ ጌታዬ ተባርክ
ተባረካ አምላኬ ተባረክ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምን ይከፈልሃል ጌታዬ (አሃሃ) ጌታዬ
ሁሉ የአንተ ነው አምላኬ (አሃሃ) አምላኬ
ምሥጋናና አምልኮ አምልኮ (አሃሃ) ምሥጋና
መቼ ይበዛብሃል ትልቅ ነህ (አሃሃ) ገናና
ቁጥር 4 · Verse 4
ተመስገንልኝ ጌታዬ ተመስገንልኝ
ከሕያዋን ጋር ሥምህን አከብራለሁኝ
ተባረክልኝ ጌታዬ ተባረክልኝ
ከሚወዱህ ጋር ሥምህን አከብራለሁኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
እንዳለፈ ውሃ መከራዬን
ረስቼዋለሁ ሳየው ጌታን
እኔስ አልሰጋም ከእንግዲህስ ብዬ
እዚህ ያደረስኝ አለ ጌታዬ
አለ ጌታዬ (አለ) (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ