Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተው ነህ ጌታዬ

Antew Neh Gietayie

2004 · ትራክ 5 · 7:16 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንተው ነህ የእኔ መታመኛ

አንተው ነህ የእኔ መደገፊያ (፪x)

እግዚአብሔር ትክክል ነው ነገር ሁሉ ለበጐ ነው

ማን ይቀራል እንባው ፈሶ ይታበሳል ቀኑ ደርሶ

መታመኛው እግዚአብሔር ማረፊያውም ከጥላው ሥር

በኩፉ ቀናት ከጐኑ ሆኖለታል በዘመኑ

አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (፪x)

ጌታዬ መተማመኛዬ (፬x)

እንዳተ ያለ መልካም ለሰው የሚራራ

የተዋረደውን ደርሶ የሚያኮራ

አላገኘሁም እኔስ እስከ እድሜዬ ልክ

እወድሃለሁኝ አንተ ነህ የኔ አምላክ

አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (፪x)

ጌታዬ መተማመኛዬ (፬x)

ቅዱስ ሥሙ እንዲጠራ ትልቅ ታሪክ በእኔ ሰራ

ጠላቶቼን አሳፍሮ ታየ ጌታ በኔ ከብሮ

አልቀረሁም እንደወደቅኩ ጌታን ይዤ መቼ አፈርኩ

አጥር ቅጥሩን እየዘለልኩ እኖራለሁ እያመለኩ

አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (፪x)

ጌታዬ መተማመኛዬ (፬x)

አቅም ጉልበት ስለሌለው የት ይደርሳል የተባለው

ዛሬ ታዲያ ለዚህ ክብር ለዚህ ሹመት ማን አበቃው

ጌታ እኮ ነው የእርሱ ተስፋ መድረሻ አለው እንዳይጠፋ

ያግዘዋል የታመነው ያኮራዋል የሚያመልከው

አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (፪x)

ጌታዬ መተማመኛዬ (፬x)

ቅዱስ ሥሙ እንዲጠራ ትልቅ ታሪክ በእኔ ሰራ

ጠላቶቼን አሳፍሮ ታየ ጌታ በእኔ ከብሮ

አልቀረሁም እንደወደቅኩ ጌታን ይዤ መቼ አፈርኩ

አጥር ቅጥሩን እየዘለልኩ እኖራለሁ እያመለኩ

አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (፪x)

ጌታዬ መተማመኛዬ (፬x)

እንዳንተ ያለ መልካም ለሰው የሚራራ

የተዋረደውን ደርሶ የሚያኮራ

አላገኘሁም እኔስ እስከ እድሜዬ ልክ

እወድሃለሁኝ አንተ ነህ የእኔ አምላክ

አንተው ነህ ጌታዬ መተማመኛዬ (፪x)

ጌታዬ መተማመኛዬ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ