ይላል ገና
Yilal Gena
2004 · ትራክ 1 · 6:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምላኬ እድሌ ፈንታዬ
ያለመለምከው ተስፋዬን
መሞት ሲገባኝ ኩነኔ
እኔስ ገረመኝ መዳኔ (፪x)
ገረመኝ መዳኔ መዳኔ ገረመኝ መዳኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ውለታ ያለበት መች ውስጡ ዝም ይላል
እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል
ፍቅሩን የቀመሰ መች ውስጡ ዝም ይላል
እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል
ያደረግልኝን ጌታ ይሆነልኝን
አስቤው ያን ዘመን በርሱ ያለፍኩትን
ክበር ልበለው እየደጋገምኩኝ
ንገሥ ልበለው እየደጋገምኩኝ
ክበር ልበለው አከብረዋለሁኝ
ንገሥ ልበለው አነግሰዋለሁኝ
ቅጥቅጥ ሸንበቆ አትሰብርም
የወደቀ አይተህ አታልፍም
አልቀረሁ ምስኪን ተብዬ
ባንተ ሰው ሆንኩኝ ጌታዬ (፪x)
ሰው ሆንኩኝ ጌታዬ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቃሉን ያሰበ መች ውስጡ ዝም ይላል
እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል
ከሞት ያመለጠ መች ውስጡ ዝም ይላል
እየደጋገመ ምሥጋና ያሰማል
ያደረግልኝን ጌታ ይሆነልኝን
አስቤው ያን ዘመን በርሱ ያለፍኩትን
ክበር ልበለው እየደጋገምኩኝ
ንገሥ ልበለው እየደጋተምኩኝ
ክበር ልበለው አከብረዋለሁኝ
ንገሥ ልበለው አነግሰዋለሁኝ
አዝማች · Chorus
ቤቴ በክብሩ ተሞላና
እኔም ወግ አየሁ እንደገና (፪x)
ምሥጋና ምሥጋና ዝማሬ ዝማሬ
ሳልሰለች በደስታ ልዘምር ለጌታ
ከሆንኩለት በላይ ምነው በሆንኩለት (፫x)
ሕይወቴ ያማረው እርሱን ያገኘሁ እለት (፫x)
አንደበቴን ልክፈት በብዙ ምሥጋና (፫x)
በቅቶኝ አልቀመጥ ውስጤ ይላል ገና (፫x)
ውስጤ ይላል ገና ውስጤ ይላል ገና
ይላል ገና ውስጤ ይላል ገና (፪x)
ይላል ገና ምሥጋና
ይላል ገና ገናና
ይላል ገና አምልኮ
ይላል ገና ዝማሬ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ