ጌታ አለ ከጐኔ
Gieta Ale Kegonie
2004 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሲሰማ ፉከራው ሽለላው የጠላቴ ወሬ
(አሃሃ) የጠላቴ ወሬ (፪x)
ሰው የሚተርፍ አይመስልም እኔ ግን አለሁ እስከዛሬ
(አሃሃ) አለሁ እስከዛሬ (፪x)
ተዉኝ ሌላ አልሰማም ቢፎክር ሁሉም ለጊዜው ነው
(አሃሃ) ሁሉም ለጊዜው ነው (፪x)
የሚያስፈራም ሆነ የሚያስደነግጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው
(አሃሃ) እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ያረገውን አስቤ ከልቤ ኦ ከልቤ
ቁጥር 2 · Verse 2
ማደሪያው ዙፋኑን ከብቤ ኦ ከብቤ
ምሥጋና አምልኮ እላለሁ
እኔማ መች ጠገብኩ ረካሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አለኝ ብዙ ሥራ ልነሳ ተረኛ ነኝ እኔ
(አሃሃ) ተረኛ ነኝ እኔ (፪x)
አትበሉ የልጅ ነገር እዩ እንጂ ጌታ አለ ከጐኔ
(አሃሃ) ጌታ አለ ከጐኔ (፪x)
የሚመችም ባይሆን ቢከፋ ቢበዛም ውጊያዉ
(አሃሃ) ቢበዛም ውጊያዉ (፪x)
እኔ አልመለስም ፈርቼ ጌታን ይዣለሁ
(አሃሃ) ጌታን ይዣለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ያረገውን አስቤ ከልቤ ኦ ከልቤ
ቁጥር 4 · Verse 4
ማደሪያው ዙፋኑን ከብቤ ኦ ከብቤ
ምሥጋና አምልኮ እላለሁ
እኔማ መች ጠገብኩ ረካሁ
ምሥጋና አምልኮ እላለሁ
ለኔማ ብዙ ነው የሆንከው
ቁጥር 5 · Verse 5
የክብሩ ደመና መንፈሱ በላዬ አለፈ
(አሃሃ) በላዬ አለፈ (፪x)
ጓዙን ጠቀለለ ሃዘኔ ባንተ ተገፈፈ
(አሃሃ) ባንተ ተገፈፈ (፪x)
የሰማዩ አዋጅ ዜናው ለኔ ምስራች ነው
(አሃሃ) ለኔ ምስራች ነው (፪x)
ምንም ነገር ባይኖር አምላኬ ከበቂ በላይ ነው
(አሃሃ) ከበቂ በላይ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ያረገውን አስቤ ከልቤ ኦ ከልቤ
ቁጥር 6 · Verse 6
ማደሪያውን ዙፋኑን ከብቤ ኦ ከብቤ
ምሥጋና አምልኮ እላለሁ
እኔማ መች ጠገብኩ ረካሁ (፪x)
ምሥጋና አምልኮ እላለሁ
ለኔማ ብዙ ነው የሆንከው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ