ጌታ ሲናገር
Gieta Sinager
2004 · ትራክ 2 · 5:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የደረቁ አጥንት ተስፋ የሌላቸው
ለክብር ሆኑ ዛሬ ለምልመው
ያለቀ ጉዳይ የሞተ ነገር
ሕይወት ያገኛል ጌታ ሲናገር
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ ጌታ ሲናገር (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እጄን ባፌ ላይ አስጭኖኛል
ጌታ ለኔ ሲል ሁሉን ሆኗል
ለመጣብኝ ሞት ራሱን ሰጥቶ
ሰው አደረገኝ ለእኔ ሞቶ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ኧረ እንዴት ልርሳ
ለእኔ የሆነው እጅግ ብዙ ነው
ምነው ዘወትር ቃሎቼ በዝተው
ጌታን ባመልከው
አዝማች · Chorus
ጌታን ባመልከው (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከፊቴ ይሰበር የብረት መዝጊያ
ጠንካራ አላውቅም ከኢየሱስ ወዲያ
አውቆ ይከፈታል ኃይልም አልጨርስ
ሥሙ ሲጠራ የአዳኜ ኢየሱስ
ቁጥር 6 · Verse 6
ኢየሱስ አዳኜ ኢየሱስ (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
እጄን ባፌ ላይ አስጭኖኛል
ጌታ ለኔ ሲል ሁሉን ሆኗል
ለመጣብኝ ሞት ራሱን ሰጥቶ
ሰው አደረገኝ ለኔ ሞቶ (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
ኧረ እንዴት ልርሳ
ለእኔ የሆነው እጅግ ብዙ ነው
ምነው ዘወትር ቃሎቼ በዝተው
ጌታን ባመልከው
አዝማች · Chorus
ጌታን ባመልከው (፬x)
ቁጥር 9 · Verse 9
እኔስ ተስፋ አልቆርጥ በሬን ዘግቼ
እንባም አይወጣኝ ሞቱን ሰምቼ
መቃብር ከፍቶ ድንጋይ ፈንቅሎ
ተነሳ ኢየሱስ ጀግና ተብሎ
ቁጥር 10 · Verse 10
ኢየሱስ ጀግና ተብሎ (፬x)
ቁጥር 11 · Verse 11
እጄን ባፌ ላይ አስጭኖኛል
ጌታ ለእኔ ሲል ሁሉን ሆኗል
ለመጣብኝ ሞት ራሱን ሰጥቶ
ሰው አደረገኝ ለእኔ ሞቶ (፪x)
ቁጥር 12 · Verse 12
ዝናህን ከሩቅ ስለ አንተ ሥራ
ሁሉም ሲያወራ
ሰምቼ አልቀረሁ እንዲያው በወሬ
አየሁህ ዛሬ
ቁጥር 13 · Verse 13
አየሁህ ዛሬ (፬x)
ቁጥር 14 · Verse 14
እጄን በአፌ ላይ አስጭኖኛል
ጌታ ለእኔ ሲል ሁሉን ሆኗል
ለመጣብኝ ሞት ራሱን ሰጥቶ
ሰው አደረገኝ ለእኔ ሞቶ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ