Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በቃሉ የሚገኝ

Beqalu Yemigegn

2004 · ትራክ 6 · 6:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተስፋ ርቆ ሲዞር የሚደግፍ ጠፍቶ

ዘንበል የሚል ማነው እንደጌታ ራርቶ

ጊዜ ወቅቱን አይተው ሰዎች ሲቀየሩ

ጌታ ግን ታማኝ ነው ወረት የለው ፍቅሩ (፪x)

መሽቶ እስኪነጋ እስኪነጋ እስኪነጋ

ያለውን ሊፈጽም የሚተጋ የሚተጋ

አላየሁኝም በቃሉ የሚገኝ የሚገኝ

አምላኬ ብቻ ብቻውን ታማኝ (፪x)

ታማኝ ነዉ ታማኝ ጌታ

ታማኝ ነዉ ታማኝ (፪x)

ጌታዬ በአንተ ምኞቴ የልቤ ደረሰ

አንተን መታመኔ እኔ መች ከንቱ ነበረ (፪x)

እሰዪ የልቤ ደረሰ

ምርኮዬ በእርሱ ተመለሰ

ተሞላ ልቤ በደስታ

ልዘርም ታማኝ ነው ጌታ (፪x)

ታማኝ ነዉ ታማኝ ጌታ

ታማኝ ነዉ ታማኝ (፪x)

እንግዲህ ምን ልበል ጨለማዬ በራ

ከሸለቆ ወጣሁ ቆምኩኝ በተራራ (፪x)

ጌታዬ ባንተ ምኞቴ ያሰብኩት ተሳካ

አንተን መታመኔ እኔ ልክ ነበር ለካ (፪x)

ልክ ነው ጌታዬ ልክ ነው

እንዳለው ነው ለኔ ያደረገው

ሁኔታ ቃሉን አለወጠው

በእውነትም ጌታዬ ታማኝ ነው (፪x)

መሽቶ እስኪነጋ እስኪነጋ እስኪነጋ

ያለውን ሊፈጽም የሚተጋ የሚተጋ

አላየሁኝም በቃሉ የሚገኝ የሚገኝ

አምላኬ ብቻ ብቻውን ታማኝ

ታማኝ ነዉ ታማኝ ጌታ

ታማኝ ነዉ ታማኝ (፪x)

በሀሩሩ ጥላ ብርሃን በጨለማ

ምስኪን የምታግዝ ፀሎት የምትሰማ

በሀሩሩ ጥላ ብርሃን በጨለማ

እኔን የምታግዝ ፀሎት የምትሰማ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ