ትክክል እውነተኛ
Tekekel Ewnetegna
2004 · ትራክ 8 · 4:24 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምኜው አልከዳኝም
በእኔ ላይ አልፈረደም (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር የእኔ ዳኛ
ትክክል እውነተኛ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው ፊትን አይቶ ሲፈርድ ጌታ ግን የልብን ነው
ሁሉንም እንደስራው አይቶ ነው የሚከፍለው
በፍርዱ አይጸጸት ለካ እንዲህ ነበር አይል
አስተዋይ ጥበበኛ እርሱ ነው የኔ ዳኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር የእኔ ዳኛ
ትክክል እውነተኛ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ክንደ ብርቱ ተቀምጦ በችሎቱ
አይፈራ አያዳላ አይዋሽም እንደሌላ
አፉ በፍርድ አይስት ሚዛኑ ትክክል ነው
በእኔ ላይ ሳይሆን ለእኔ ፈረደልኝ መድህኔ
ዳኛዬ እሱ ነው የእኔ ዳኛ (፬x)
በግራና በቀኙ አማካሪ አይፈልግም
ቃሉንም የሚያርመው ከቶ አንድም አይገኝም
እግዚአብሔር አዋቂ ነው ሥራውን ይመዝናል
ውሳኔው መጨረሻው የእኔን ልብ አሳርፏል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር የእኔ ዳኛ
ትክክል እውነተኛ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ