Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የደስታ መንፈስ

Yedesta Menfes

2004 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እኔስ በአምላኬ በጌቶች ጌታ

ይህ ነው አይባልም ያለኝ ደስታ

ደመና ሳይኖር በአካባቢዬ

ግራ ተጋብቷል ጠላት በደስታዬ (፫x)

የደስታ መንፈስ በላዬ ወርዶ

ሃዘን ምሬቴን ከውስጤ ወስዶ

አመልከዋለሁ ከጠዋት ማታ

ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ደስታ (ጌታ) (፬x)

የደስታዬ ምንጭ ኢየሱስ ሆኖ

ሃዘኔ ጠፋ እንደጉም በንኖ

አላማርርም አላንጐራጉር

ደስተኛ ነኝ ሁሌ በእግዚአብሔር (፫x)

የደስታ መንፈስ በላዬ ወርዶ

ሃዘን ምሬቴን ከውስጤ ወስዶ

አመልከዋለሁ ከጠዋት ማታ

ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ደስታ (ጌታ) (፬x)

ማን ደስ ሊለው እኔ ልከፋ

በትንሽ ትልቁ ደስታዬ አይጠፋ

ለጠላት ወሬ ጆሮም አልሰጠው

ደስታዬ ፍጹም መቼም ማይወሰድ ነው (፫x)

የደስታ መንፈስ በላዬ ወርዶ

ሃዘን ምሬቴን ከውስጤ ወስዶ

አመልከዋለሁ ከጠዋት ማታ

ኢየሱስ እኮ ነው የኔ ደስታ (ጌታ) (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ