Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የእኔ ጌታ እወድሃለሁ

Yenie Gieta Ewedihalehu

2004 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንዴት ልርሳህ እንዴት ችዬ

ፍቅርህ ብዙ ነው ጌታዬ (፪x)

የእኔ ጌታ እወድሃለሁ

በአንተ ብርታት ሰው ሆኛለሁ

በከበረው ሠረገላ

ያስቀመጠኝ/ያሰበኝም የለም ከአንተ ሌላ (፪x)

መማለጃ አትፈልግ እጅ መንሻ

ለምህረትህ የለህ መጨረሻ

እንዲያው ወደኸኝ ነው ወግ ያየሁት

በከፍታ ስፍራ የወጣሁት (፪x)

የእኔ ጌታ (የእኔ ጌታ) እወድሃለሁ (እወድሃለሁ)

በአንተ ብርታት ሰው ሆኛለሁ

በከበረው (በከበረው) ሠረገላ (ሠረገላ)

ያስቀመጠኝ የለም ከአንተ ሌላ

ምክንያት ሰበብ ፈላልጌ

ልሰዋለት ለአምላኬ (፪x)

የእኔ ጌታ (የእኔ ጌታ) እወድሃለሁ (እወድሃለሁ)

በአንተ ብርታት ሰው ሆኛለሁ

በከበረው (በከበረው) ሠረገላ (ሠረገላ)

ያስቀመጠኝ/ያሰበኝም የለም ከአንተ ሌላ (፪x)

ከመኳንንት ጋራ አስቀመጥከኝ

የክብርህን ዙፋን አወረስከኝ

ምንም የለም ለኔ ያላረከው

ከነገሮች በላይ እወድሃለው (፪x)

የእኔ ጌታ (የእኔ ጌታ) እወድሃለሁ (እወድሃለሁ)

በአንተ ብርታት ሰው ሆኛለሁ

በከበረው (በከበረው) ሠረገላ (ሠረገላ)

ያስቀመጠኝ/ያሰበኝም የለም ከአንተ ሌላ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ