አምንሃለሁ
Amnehalehu
2013 · ትራክ 13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምንሀለሁ ጌታ አምንሀለሁ
አምንሀለሁ ኢየሱስ አምንሀለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሠማይ ምድር ያልፍል ቃሌ ግን አያልፍም
ከአፌ የወጣዉ ቃል እንዲሁ አይመለስም
ብለህ እንደተናገርህ ቃልህን ፈጸምከዉ
ኮራሁብህ ኢየሱስ አንተ በሰራኸዉ
ብታደርግ ልክ ብታፈርስ ልክ
የማትሣሣት ፍፁም የሆንክ
አንተ ሥራ እንጂ ቃልህን ላክና
ሚከለክልህ የቱ ነው ጀግና ከአንተ ወዲያ ጀግና
አዝማች · Chorus
አምንሀለሁ ጌታ አምንሀለሁ
አምንሀለሁ ኢየሱስ አምንሀለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁኔታ ሚሰብከኝ ሚያስፈራ ነገር ነው
የሚታየው ሁሉ እጅግ አስደንጋጭ ነው
ቃልህ ትዝ ሲለኝ አይዞህ ነው የሚለኝ
እንዳልፈራ እንዳልዝል ነው የሚያስታውስኝ
መች በሰው ስሌት በአዋቂ መላ
ሆኖ ያውቅና የአንተ እኮ ሌላ
ዛሬ ርሃብ ሆኖ ነገ ጥጋብ ነው
ሥትል አምናለሁ ሁሉ የአንተ ነው
ሁሉ በእጅህ ነው
አዝማች · Chorus
አምንሀለሁ ጌታ አምንሀለሁ
አምንሀለሁ ኢየሱስ አምንሀለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ውጣ ያልከኝ አንተ እንሆ ምድሪቷ
ሥሜን አውጅባት በርዝመት ስፋቱዋ
አብሬህ እሆናለሁ እስከ መጨረሻው
ሥትል ተቀበልኩኽ ካሳብህ ተስማማሁ
እንደ አባቶቼ በአንተ ታምኜ
እራሴን ክጄ በዓለም ጨክኜ
ከኖሩስ አይቀር እንዲህ ነው ኑሮ
አንተን አክብሮ ደሞ አስከብሮ (፪x)
ዛሬም ተመለክ አንተ አምላክ ነህ
ዛሬም ተደነቅ አንተ ድንቅ ንህ
ዛሬም ተወደስ አንተ ጀግና ነህ
ዛሬም ተሞገስ አንተ ልዩ ነህ
ሲያንሥህ ነው ጭብጨባ (፬x)
ሲያንሥህ ነው ዕልልታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ