Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክበር

Keber

2013 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እራሴን በራሴ እንዳላስገኘሁኝ

በአንተ እንደተሰራሁ ለአንተም እንደሆንኩኝ

ይገባኛል እና እዘዝ በህይወቴ

ከልካይ የለብህም የአንተ ነው እኔነቴ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ</u > (፫x) የእኔ ጌታ

የምቆጥበው የምሰስተው

ክብር የለኝም ሁሉ የአንተ ነው (፪x)

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ</u > (፫x) የእኔ ጌታ

ከአንተ ወዲህ ገዢ ከአንተ ሌላ አባት

ማን ሊነግስ ይወዳል ነፍሴንስ ሊሞላት

እኔ እንደው የአንተ ነኝ በደም የገዛኽኝ

የፍቅርህ ምቾቱ ሌላም አያሰኘኝ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

ክብር የማይገባኝ ያኔ ሳለው ከንቱ

ማነው የከፈለልኝ እዳዬን በሞቱ

ኢየሱስ አይደለህ ወይ ወርደህ ያነሳኽኝ

ታዲያ ክብሬ የቱ ነው ሁሉን ለአንተ አልኩኝ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

በምስጋና ቅኔ ውዳሴ በመዝሙር

እጨምራለሁኝ ይሁን ለአንተ ክብር

ምኞቴ የስምህ ክብር መታሰቢያህም ነው

በቀንም በሌትም ናፍቆቴ ይሄ ነው

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

የምቆጥበው የምሰስተው

ክብር የለኝም ሁሉ የአንተ ነው (፪x)

ክበር (፫x) የእኔ ጌታ

ንገስ (፫x) የእኔ ጌታ

በምን ዓይነት ዜማ በምን ዓይነት

በብዙ ዓይነት ዜማ በብዙ ዓይነት

በምን ዓይነት ግጥም በምን ዓይነት

በብዙ ዓይነት ግጥም በብዙ ዓይነት (፪x)

ባመሰግንህ ይበቃል አልልም

እንዲያንስህ አውቃለው ይህ ለአንተ ትንሽ ነው (፬x)

ይህ ለአንተ ትንሽ ነው (፲x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ