በምህረትህ
Bemehereteh
2013 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሳተ ይመለስ የለም ወይ ከግድፈቱ
የወደቀስ ይጠገን የለም ወይ ከስብራቱ
አይኖቹን ሲያቀና በተስፋ ወደአንተ
ሲማፀን ምህረትን እየወተወተ
አይችልም መጨከን አንጀትህ የአባትነትህ
አጥበህ ታነፃለህ
አንተ ፍቅር ነህ
ይሄንን ላውራልህ
አዝማች · Chorus
ብደክም ወድቄ እንዳልቀር ፀጋህ ብዙ ነው ያግዘኛል
ምህረትህ ከቁጣ ይፈጥናል እንድኖር ምክንያት ሆኖኛል
አልመካም መች ቆሜ ባቅሜ
ባትረዳኝ ሆነህ አጠገቤ ከጐኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በጨለማ ብቀመጥ ብርሀኔ ነህ
የሀጢያት ሸክም ቢያጐብጠኝም ታቀናኛለህ
ተስፋዬ ይቅርታ መጽናኛዬም ፊትህ ነው
ስለቸርነትህ ብቻ ነው ምኖረው
ሲሰማኝ መኖርህ ሳስተውል መገኘትህን
መንፈሴ ያንስራራል
ነቅቶ ያዳምጥሀል
ጌታዬና አምላኬ ይልሃል
አዝማች · Chorus
ብደክም ወድቄ እንዳልቀር ፀጋህ ብዙ ነው ያግዘኛል
ምህረትህ ከቁጣ ይፈጥናል እንድኖር ምክንያት ሆኖኛል
አልመካም መች ቆሜ ባቅሜ
ባትረዳኝ ሆነህ አጠገቤ ከጐኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጉስቁልናዬን ስታይ አዘንክልኝ
እራርተህ እጅህን ዘረጋህ አቅፍህ ልታነሳኝ
ግድ የሚልህ ለኔ መጥፋቴን ማትወደው
ፊትህ ለኔ በራ በደሌንም ተውከው
እንደባሪያ መሆን ሳያንሰኝ አንተ ግን ልጅ አልከኝ
እራሴን ልስጥህ ዝቅ ልበልልህ
ላንተው ኖሬ ላንተው ልሙትልህ
አዝማች · Chorus
ብደክም ወድቄ እንዳልቀር ፀጋህ ብዙ ነው ያግዘኛል
ምህረትህ ከቁጣ ይፈጥናል እንድኖር ምክንያት ሆኖኛል
አልመካም መች ቆሜ ባቅሜ
ባትረዳኝ ሆነህ አጠገቤ ከጐኔ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በምህረትህ ብዛት ቤትህ እገባለሁ (፪x)
ስለምህረትህ ጌታ አመልክሃለሁ (፪x)
በፊትህ ሞገስ ያገኘሁት
አይደለም በእራሴ ያቆሙኩት
የፅድቅ የሥራ መልካም ነገር
ምህረትህ ድፍረት ሆኖልኝ ነው
የፀጋህ ማስቻሉ በዝቶልኝ ነው
ስምህን ላክብረው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ