Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ስለ አምላክነትህ

Seleamlakeneteh

2013 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለ አምላክነትህ ስለ ጌትነትህ

ስለ እጆችህ ስራ ባወራው ባወራ

አያልቅ የአንተ ሥራ (፪x)

አያልቅ የአንተ ስራ (፬x)

ሰባቱን ከዋክብት ኦርዬንን የሰራ

ጨለማውን ንጋት ብርሀን የሚያበራ

ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርገው

ስራው እንዲህ ያማረው ስሙ እግዚአብሔር ነዉ (፪x)

ስለ አምላክነትህ ስለ ጌትነትህ

ስለ እጆችህ ስራ ባወራው ባወራ

አያልቅ የአንተ ሥራ (፪x)

አያልቅ የአንተ ስራ (፬x)

ውሆችን በእፍኙ የሰፈረ ጌታ

ሰማይንም ደግም በስንዝር የለካ

ኽረ እግዚአብሔርን የአማከረው ማነው

ማስተዋሉ ረቂቅ ኃይሉ እጅግ ብዙ ነው (፪x)

ስለ አምላክነትህ ስለ ጌትነትህ

ስለ እጆችህ ስራ ባወራው ባወራ

አያልቅ የአንተ ሥራ (፪x)

አያልቅ የአንተ ስራ (፬x)

በዓመታት መሀል ስራን ትሰራለህ

ሁኔታ አያግድህ ከሁኔታ በላይ ነህ

አቤት ይሄ ጌታ እኔ የማመልከው

ለዘላለም ነዋሪ መለወጥ የማያውቁው (፪x)

ስለዚህ ላምልከው በሀሴት ውሰጥ ሆኜ

የማይለወጠውን ስላገኘች ነፍሴ

ከቤቱ በረከት ስለረካች ነፍሴ (፪x)

ከእርሱ ሌላ አልፈልግም

እርሱ ለእኔ ምኞቴ ነው

ርሀቤም ጥማቴም የሆነው

ከእርሱ ሌላ አልፈልግም

እርሱ ለእኔ መሻቴ ነው

ርሀቤም ጥማቴም የሆነው

ርሀቤም ጥማቴም የሆነው (፲፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ