ማረኝ
Maregn
2013 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እጅህ አላጠረም ከመስራት
ድምጽህ አልደከምም ከመጥራት
ይልቅ በበደሌ ያሳዘንኩህ እኔ
ማስተዋል ያቃተኝ በቃልህ ስትነግረኝ
ስለዚህ አምልኮዬ ሆነ አንካሳ
አንዳች ጠብ አይልም በስምህ ብወቅድ ብነሳ
አዝማች · Chorus
ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የእኔ ነው ጠብና ክርክር
ከአንተ ይልቅ መፈለግ የራስ ክብር
የተጋረደ ነው በእኔ ያለው ብርሀን
እንቅፋት ሆኛለሁ ስለ ሌሎች መዳን
ኑሮዬ ምልክት የለውም የአንተነት
ሥጋዬ በርትቶአል መንፈሴ ግን ደክሟል
አዝማች · Chorus
ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
አይታዘዝ ልቤ ጠማማ
ምላሴ አይደንግጥ ሲያማ
ወገኑን የማይወድ ቂመኛ ልብ ያለው
ትዕቢት የተሞላ ከኔ ሌላ ማነው
የቀደሙወን ፍቅር ከጣልኩት በጣም ቆይቻለሁ
ሰው ሲያየኝ የቆምኩኝ ብመስልም እኔስ ወድቂያለሁ
አዝማች · Chorus
ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁለንተናዬ ግልጽ በፊትህ
አንዳች እንኳን የለ ማልነግርህ
ከእግርህ ስር ወድቃለሁ እስከነህ ኃጢያቴ
በደምህ ታመኜ ዳግም ለመንፃቴ
እባህክ ስለ ስምህ ብለህ ራራልኝ
በቀራንዮ መስቀል በከፈልከው ዋጋ አስበኝ
አዝማች · Chorus
ማረኝ ማረኝ ጌታ ማረኝ (፪x)
ማረኝ ማረኝ ኢየሱስ ማረኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
አንደገና እንደ አዲስ ሃይልን እሞላለሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
በንስሀ ፍሬያማ ህይወት እኖራለሁ
ቁጥር 7 · Verse 7
ፀጋህ ይበዛለኛል ቃልህ እበላለሁ
መንፈስህን ጠጥቼ የልብህ ሰው እሆናለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ