Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ትመቸኛለህ

Temechegnaleh

2013 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ትመቸኛለህ ጌታዬ

ትመቸኛለህ ኢየሱስ (፪x)

ከእናት ማህፀን እስከ ሽመግልና ድረስ

ምተሸከም አምላክ ቃልህን ማታፈርስ

ፍፁም ነው ፍቅርህ የሱስ ያለ እንከን የሆነ

የኽው ተስፋ ያለው ሠው አረከኝ ህይወቴ ሰከነ (፪x)

ትመቸኛለህ ጌታዬ

ትመቸኛለህ ኢየሱስ (፬x)

በዓለም ሣለሁኝ ከአለም ተለይቼ ልኖር

ከንቱ እንደሆነ አውቄ የዚህች ምድር ክብር

ስደክም ስበረታ በህይወት መንገድ ላይ

ክንዶች ያሣረፈኝ የደላኝ የለም ካንተ በላይ

ትመቸኛለህ ጌታዬ

ትመቸኛለህ ኢየሱስ (፬x)

ሳልወድ ወይም ሣልሮጥ ምህረትን አግኝቻለሁ

ነፍሴን አርክተሀት ልዩ ሰው ሆኜአለሁ

መቅበዝበዜ አሣዝኖህ ፈልገህ አግኝተኽኝ

ከቶ እንዳይጠማኝ የሕይወትን ውሃ አጠጣኽኝ

ትመቸኛለህ ጌታዬ

ትመቸኛለህ ኢየሱስ (፬x)

የልቤ ፍሰሀ አምላኬና አባቴ ለኔ

መቼም የማትተወኝ ማገኝህ ከጐኔ

ምላሴ ሲያከብርህ በሚችለው ሁሉ

የአካል ክፍሎቼ ተባብረው በደስታ ያመልካሉ

ትመቸኛለህ ጌታዬ

ትመቸኛለህ ኢየሱስ (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ