ምህረትን ትወዳለህ
Mehereten Tewedaleh
2013 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመንገድህ አግኘኝ ጌታ እንደ ሀሳብህ
ለትጐበኘኝ ስትመጣ እንዳልጠፋ ከፊትህ
ፀጋህን አብዛልኝ ኢየሱስ በሕይወቴ
መንፈስህ ያግዘኝ ይጽና መሰረቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትን ትወዳለህና
ብርታትን ትሰጣለህና
እኔም ልታሰብ ጌታ
ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ
ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ
ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለ እኔ ነፍስህን ልትሰጥ አልሰሰትክምና
እዳዬን ሁሉ ልትከፍል ተችሎሀልና
እኔም ለመውደድህ ልሁን እንደልብህ
አንተን መፍራት ሙላኝ ዝቅ ልበልልህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትን ትወዳለህና
ብርታትን ትሰጣለህና
እኔም ልታሰብ ጌታ
ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ
ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ
ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን
ቁጥር 3 · Verse 3
በመቅደስህ ቀድሰኝ በእሣትህ አንጥረኝ
የማትወደው ከእኔ ይቆረጥ እንዳሻህ አበጃጀኝ
ለእኔም የሻለኛል በእጅህ መቀረፁ
ኋላ ሞልቶ ይፈሣል ከአንተ በረከቱ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትን ትወዳለህና
ብርታትን ትሰጣለህና
እኔም ልታሰብ ጌታ
ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ
ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ
ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን
ቁጥር 4 · Verse 4
ድንጋዩ ልብ ከእኔ ይውጣ ስጋ ይሁንልኝ
የቀናውን መንፈስህን በውስጤ አድስልኝ
ክርስቲያን ከተባልኩ በአንተ ከተጠራሁ
እንደ ሀሳብህ ኖሬ ማለፍን እሻለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትን ትወዳለህና
ብርታትን ትሰጣለህና
እኔም ልታሰብ ጌታ
ኃይል ይብዛልኝ ልበርታ
ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ
ከፍ ያድርግህ ያክብርህ አሜን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ