Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ላመስግንህ

Lamesgeneh

2013 · ትራክ 12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የህይወቴ እስትንፋስ በእጅህ መዳፍ ውስጥ ነው ያለው

ያለ አንተ መኖር አልችልም በእርግጥ ሞቼ እቀራለሁ

ህያውነቴ ባንተ ነው በነፍሴ ጌታ

ለዘላለም ላመስግንህ ላዚም በእልልታ (፪x)

ልባርክህ ልባርክህ

ላምልክህ ላምልክህ (፪x)

በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ

በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (፪x)

ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (፪x)

አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (፪x)

ኢየሱስ (፪x)

ኢየሱስ (፬x)

አምላኬ አንተ ለእኔ መታመኛዬ አለቴ

ደስታዬ አንተን ሳስብ ነው በእርግጥ ማረፍ መርካቴ

ስለዚህ አንተን ላምልክህ ላውራ ክብርህን

የዝማሬ ጽምፅ ይሰማ ላሸብሽብልህ (፪x)

ከፍ ላርግህ ከፍ ላርግህ

ላውድስህ ላወድስህ (፪x)

በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ

በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (፪x)

ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (፪x)

አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (፪x)

ኢየሱስ (፪x)

ኢየሱስ (፬x)

እንዳንተ የሚሆን ለእኔ አላገኘሁምና

ከእናትም ከአባት ከወዳጅ በልጠህብኛልና

አምላኬ መድሀኒቴ ነህ ለእኔ ፈዋሼ

በአምላኮ አንተን ማክበር ነው ምላሼ (፪x)

ላመስግንህ ላመስግንህ

ላሞጋግስህ ላሞጋግስህ (፪x)

በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ

በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (፪x)

ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (፪x)

አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (፪x)

ኢየሱስ (፪x)

ማፍቀሬን ለአንተ ያለኝን ጥልቅ የሆነ መውደዴን

እገልፃለሁ ለስምህ ክብር በማቅረብ መስዋዕቴን

ደጋግሜ አመልክሃለሁ ይህም ያንስሀል

ያለምንም ዋጋ እንዲሁ አድነኽኛል (፪x)

ልቀኝልህ ልቀኝልህ

ላክብርህ ላክብርህ (፪x)

በአዲስ በአዲስ ቅኔ እቀኝልሀለሁ እኔ

በአዲስ በአዲስ ዜማ ድምጼ ለአንተ ይሰማ (፪x)

ከልቤ በሙሉ ሀይሌ (፪x)

አመሰግንሀለሁ ክብርን ለአንተ እሰጣለሁ (፪x)

ኢየሱስ (፪x)

ኢየሱስ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ