ክንደ ብርቱ
Kende Bertu
2013 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አበቃ አከተመ አይሆንም በተባለበት
የጌታ ስም ሲጠራ ሁሉ ይዘራል ህይወት
ያለአንዳች እርዳታ ብቻውን ድንቅን አድርጐ
ልጆቹን ያሣርፋል በሀይሉ ተገለጦ
ታላቅነቱ አይወሰን ከ እስከ አይባልም
ብቻ እርሱ ይስራ እንጂ ማንም ፊቱ አይቆምም (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታችን ክንደብርቱ ነው (፫x)
የለም ሚገዳደረው አርሱ ብርቱ ነው
ኢየሱስ አሸናፊ ነው (፫x)
ማነው የሚቋቋመው አሸናፊ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጽኑ ግንብ በጠላት ፊት የማይደፈር መከታ
ከክፋት ከሰይጣን እጅ የሚከልል ጌታ
ነው እኛ ምናመልከው ሀይለኛና ባለስልጣን
ተጠግተነው አርፈናል መደገፊያ ሆኖልን
ጥበቃው እጅግ ያስደንቃል ልጆቹን ያሳርፋል
ሀይሉም ከቶ አይደክምም በሰልፍ ይበረታል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታችን ክንደብርቱ ነው (፫x)
የለም ሚገዳደረው አርሱ ብርቱ ነው
ኢየሱስ አሸናፊ ነው (፫x)
ማነው የሚቋቋመው አሸናፊ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ከርሱ ጋር የሆነ ኽረ ሌላ ምን ያሻዋል
ከክንፎቹ በታች ሆኖ ተማምኖ ይኖራል
በክፉ ቀን አይሰጋም አምላኩ ይታደገዋል
ከረግረግ ከጭቃ አውጥቶ በአለት ያቆመዋል
ዛሬም ይህ ጌታ ከእኛ ጋራ ካለ ምንደነው የሚያስፈራን
በእርሱ እየተማመንን በድል እንሄዳለን (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታችን ክንደብርቱ ነው (፫x)
የለም ሚገዳደረው አርሱ ብርቱ ነው
ኢየሱስ አሸናፊ ነው (፫x)
ማነው የሚቋቋመው አሸናፊ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከጌታ የተነሳ በህይወት መኖር ችለናል
ካስጨናቂዎቻችን ሁሉ በእርሱ አርፈናል
ማዳኑን የክንዱን ብርታት ባይናችን አሣይቶናል
ስለዚህም ልናከብረው ወደ እርሱ መጥተናል
ለክበሩ እንዘምራለን እናመሰግነዋለን
ጌታ ስለሚገባው እናመልከዋለን (፪x)
ምስጋና ለርሱ ይገባዋል (፫x)
ሌላ ምን ይሰጠዋል ለርሱ ይገባዋል (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ