ሃሌሉያ
Hallelujah
2013 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማስተዋልህ በሊቅ አትመረመርም
እግዚአብሄር ታላቅ ነህ ማንም አላየህም
በላይ በከፍታ በክብር ትኖራለህ
በበረከትህም ምድርን ታጠግባለህ
ባለጠግነትህ አይጐድልም
ይፈቃል ይፈሳል ዘላለም (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ክብር ይገባሀልና
አምሣያ የሌለህ ሁሉን ቻይ ነህና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የፊትህ ብርህን ከፀሐይ ይደምቃል
ሰባቱን ከዋክብት በእጆችህ ይዘሀል
አይኖችህ እንደ እሣት ነበልባሎች ናቸው
የራስህም ፀጉር ከነጭም ነጭ ነው
ማን መቆም ይችላል ካንተ ጋር
አይቶ ነፍስ ማን ይቀርለታል (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ክብር ይገባሀልና
አምሣያ የሌለህ ሁሉን ቻይ ነህና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መላዕክት በፍርሀት ወድቀው ይሰግዱልሀል
ያምልኮአቸው ሽታ ቤትህን ሞልቶታል
ክብርና ውዳሴ ምስጋና ይገባሀል
እያሉ እራቱ እንስሶች ያከብሩሀል
ሽማግሌዎች ወድቀው የሰግዱልሀል
በፈቃድህ ሁሉን ፈጥረሀል
እያሉ ክብራቸውን ይሰጡሀል
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ክብር ይገባሀልና
አምሣያ የሌለህ ሁሉን ቻይ ነህና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ