Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አየሁ

Ayehu

2013 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አየሁ እኔስ እኔስ አየሁ

በዚህች እድሜ ስንቱን አየሁ

በዙፋኑ ፀንቶ ያለው

እግዚአብሔር ግን ሁሌም ያው ነው (፪x)

እግዚአብሔር ግን ሁሌም ያው ነው (፮x)

ትላንት ሲታይ ማይደፈር ሲባል ዛሬ አይን ላፈር

አንቱ መባል ትላንት አንሶት ዛሬ አንተነት ሲበዛበት

ሰው ወዶ የሾመውን ሰው ወዶ ይሸረዋል (፪x)

ከእኛ እግዚአብሔር ጋር ግን ማን ይስተካከላል

ከዘለአለምም እስከ ዘለአለም (፪x)

ነው መንግስቱ ጽኑ የሚመስለው የለም

ህያው ነው እግዚአብሔር ህያው ነው (፪x)

ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፪x)

አንድ ሺ ቀን እንደአንድ ቀን

አንድ ቀንም አንደአንድ ሺ

ሁሌ ጌታ በዘመናት

ፈጣሪያቸው ለእለታት

በጊዜ አይገደብ እርሱ እግዚአብሐር ነው (፪x)

አመቶቹ አያልቁ ጸንቶ የሚኖር ነው

ያሳልፋል እንጂ እርሱ አንደው አያልፍም (፪x)

ተላንትናም ዛሬም ያው ነው ለዘላለም

ህያው ነው እግዚአብሔር ህያው ነው (፪x)

ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፪x)

አልፋ ኦሜጋ እርሱ እኮ ነው

ለዘላለም ህያው እርሱ ነው

ላሞጋግሰው ይህን ጌታ

በጭብጨባ በእልልታ

ክብርና ሞገስም ባለጠግነትም ሊቀበል የሚገባው

ከጌቶቹ ጌታ ከእርሱ በቀር ማን ነው

ግርማው የተለየ ባለ ብዙ ዝና (፪x)

ያለ አጋር እረዳት ብቻዉን ገናና

ህያው ነው እግዚአብሔር ህያው ነው (፪x)

ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፪x)

ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፪x)

ህያው ነው እግዚአብሔር ህያው ነው (፪x)

ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ