አንተን ብቻ ባገኝ
Anten Becha Bagegn
2014 · ትራክ 10 · 3:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የልቤ አምላክ ሆይ ደስታዬ ነህ
የልቤ አምላክ ሆይ እረፍቴ ነህ
ከአንተ ውጪ ምን ምን ሕይወት አለ
ከአንተ ውዲያስ ምን ምንስ ክብር አለ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉን አግኝቼ አንተን ከማጣ
ሁሉን ነገር ኖሮኝ ክብርህ ከሚጐድልብኝ (፪x)
ሁሉን አጥቼ አንተን ብቻ ባገኝ
ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው
ሁሉን አጥቼ ኢየሱስን ባገኝ
ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ረቢ ያልኩትን ወዲያ እየጣልኩኝ
በፍፁም ልቤ አንተን እየፈለኩኝ
የሚታየውን የዓለምን ነገር
ትቼ እሮጣለሁ ላገኝ የአንተን ክብር (፪x)
አዝማች · Chorus
ሁሉን አግኝቼ አንተን ከማጣ
ሁሉን ነገር ኖሮኝ ክብርህ ከሚጐድልብኝ (፪x)
ሁሉን አጥቼ አንተን ብቻ ባገኝ
ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው
ሁሉን አጥቼ ኢየሱስን ባገኝ
ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው
ህልውናህ መገኘትህ ሃልዎትህ
ለእኔ ክብሬ ይህ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ