Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክብርህ በእኔ ላይ ይሁን

Kebreh Benie Lay Yehun

2014 · ትራክ 7 · 3:12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውኃን የተጠማ ሰው

ሳይጠጣ እንደማይረካ

እኔም ተጠምቼሃለሁ

ክብርህን ሳይ ብቻ እጠግባለሁ (፪x)

ክብርህ በእኔ ላይ ይሁን (፪x)

ኦ ክብርህ በእኔ ላይ ይሁን (፪x)

ሌላውማ አያጠግበኝ እኔን

ሌላውማ አያረካው ልቤን (፪x)

ሁሉን አየሁ ግን እንደአንተ የከበረ

አላገኘሁ አላገኘሁ (፪x)

ምን አለ በዚህ ምድር ላይ ከአንተ የሚወዳደር

ልኖርለት የሚገባኝ ከክብርህ በስተቀር

ሌላውማ አያጠግበኝ እኔን

ሌላውማ አያረካው ልቤን (፪x)

የባሕሪው ምሳሌ የክብሩ ነጸብራቅ የሆንከው

ከአባትህ እቅፍ የወጣሀው

ኢየሱስ የምሻው አንተን ነው (፫x)

የእግዚአብሔር ክብር የምሻው አንተን ነው

ኢየሱስ የምሻው አንተን ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ