መታደል ነው
Metadel New
2014 · ትራክ 12 · 4:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ እንደመኖር ያለ ኑሮ ነለም
አንተን እንደማክበር ያለ ክብር የለም
ከአንተ እንደመኖር ያለ ኑሮ ነለም
አንተን እንደማክበር ያለ ክብር የለም የለም
ፈቃድህን እንደማድረግ ያለ ስኬት የለም
በቤትህ ውስጥ እንደማደግ ያለ ደስታ የለም
አዝማች · Chorus
ኑሮዬም ይሄ ነው
ክብሬም ይሄ ነው
ስኬቴም ይሄ ነው
ደስታዬም ይሄ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በጐና ደስ የሚያሰኘውን
ፈቃድህን ፍፁም የሆነውን
አድርጐ ለዚያ ኖሮ ማለፍ
መታደል ነው በጥላህ ስር ማረፍ
እንዴት ያለ መታደል ነው መታደል ነው መታደል ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
ኑሮዬም ይሄ ነው
ክብሬም ይሄ ነው
ስኬቴም ይሄ ነው
ደስታዬም ይሄ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በአንተ ዘንድ እጅግ የከበረ
ነውና ፍጻሜው ያማረ
በሰማይ አለው ታልቅ ዋጋ
ለአንተ መኖር መኖር በአንተው ፀጋ
እንዴት ያለ መታደል ነው መታደል ነው መታደል ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
ኑሮዬም ይሄ ነው
ክብሬም ይሄ ነው
ስኬቴም ይሄ ነው
ደስታዬም ይሄ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ደስታዬም ይሄ ነው
ስኬቴም ይሄ ነው
ክብሬም ይሄ ነው
ኑሮዬም ይሄ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ