Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይኸው ልቤን

Yehew Lebien

2014 · ትራክ 9 · 6:09 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደሚቃጠል መስዋዕት በሁለንተናዬ ልሰጥ

ሩጫውን ሮጬ ልጨርስ አላማን ከግብ ላደርስ

ወስኛለሁ ቆርጬ ተነስቻለሁ

ወስኛለሁ ሕይወቴን ሰጥቼሃለሁ (፪x)

ይሄው ልቤን ይሄው ነፍሴን

ይሄው እኔን ሁለንተናዬን

እሰጥሃለሁ ክበርበት ንገስበት

የማስቀረው ነገር የለም ደብቄ ምይዘው ለእኔ

ሁሉንም ሰጥቼሃለሁ ክበርበት መድህኔ

በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍለህ ገዝተኸኛል

እኔም ደግሞ ለአንተ ልኖር ይገባኛል (፪x)

ይሄው ልቤን ይሄው ነፍሴን

ይሄው እኔን ሁለንተናዬን

እሰጥሃለሁ ክበርበት ንገስበት

በአንተ ልትልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል (፬x)

ይገባል ይገባል ይገባል ይገባል

ይገባል ይገባል ይገባል ይገባል

ይገባል ይገባል ይገባል ይገባል

ይሄው ልቤን ይሄው ነፍሴን

ይሄው እኔን ሁለንተናዬን

እሰጥሃለሁ ክበርበት ንገስበት (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ