Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አይረሳኝም

Ayeresagnem

2014 · ትራክ 2 · 4:08 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አይረሳኝም ለኔ ያደረከው ብዙ ውለታ

በመስቀል ሞተህ ዋጋ የከፈልከው በጎልጎታ

ምኔን ብታይ ምኔን ብትወደው

የቱ ህይወቴ ተመችቶህ ነው

እራስህን ለኔ የሰጠኸው (፪x)

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

ሞቴን ስጠባበቅ ህይወቴን ቀጠልከው

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

እራስህን ለኔ የሰጠኸው

ጭንቀቴን ወሰድከው ህመሜን ተካፈልከው ስለኔ ሞትክ

እርጉም ሰው ነህ ተባልክ ተገረፍክ በጅራፍ

ፃዲቅ ሆነህ ሳለህ ሆንክ ስለኔ ሀጥያት

ምኔን ብታይ ምኔን ብትወደው

የቱ ህይወቴ ተመችቶህ ነው

እራስህን ለኔ የሰጠኸው (፪x)

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

ሞቴን ስጠባበቅ ህይወቴን ቀጠልከው

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

እራስህን ለኔ የሰጠኸው

ከቶ ምን እልላለሁ እንዲህ ከወደድከኝ

ከመገረም ውጪ ምን እከፍልሃለሁ /4

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

ሞቴን ስጠባበቅ ህይወቴን ቀጠልከው

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

እራስህን ለኔ የሰጠኸው

ምኔን ብትወደው ነው (፪x)

ሞቴን ስጠባበቅ ህይወቴን ቀጠልከው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ