Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከነኃጢአቴ

Kenehatiatie

2014 · ትራክ 1 · 4:13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ነፍሴን ጨለማ ውጧት

መግቢያው መውጫው ጠፍቷት

ህይወቴ በሀጥያት ተዘፍቃ

እንኳን ልጅህ ልሆን

በቤትህ ውስጥ ልኖር

መኖር ማይገባኝ ባሪያ ነበርኩ (፪x)

ከነሀጥያቴ ወደድከኝ

ከነሀጥያቴ መረጥከኝ

ልጅህ አደረከኝ

በማይጠፋው ፍቅርህ ለወጥከኝ (፪x)

መንገዴ ተሳስቶ እዳን ተሸክሜ

በፊህ ለመሆን እጅጉን ቆሽሼ

እንኳን ልጅህ ልሆን

በቤትህ ውስጥ ልኖር

መኖር ማይገባኝ ባሪያ ነበርኩ (፪x)

ከነሀጥያቴ ወደድከኝ

ከነሀጥያቴ መረጥከኝ

ልጅህ አደረከኝ

በማይጠፋው ፍቅርህ ለወጥከኝ (፪x)

ወዶኛል አዳነኝ

በምህረቱ ሰው አረገኝ

ሞቼ ሳለሁ ከፍጥረቴ

ሕያው ሆንኩኝ በኢየሱሴ (፪x)

ከነሀጥያቴ ወደድከኝ

ከነሀጥያቴ መረጥከኝ

ልጅህ አደረከኝ

በማይጠፋው ፍቅርህ ለወጥከኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ