Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኢየሱስ ልክ

Eyesus Lek

2014 · ትራክ 12 · 4:15 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በርግጥ ቢመስልም የሌለ ዳኛ

ህይወት ስትሆን መከራ እና እንባ

በውነት ልክ ነው እርሱ አይሳሳትም

ቅን ፈራጅ አምላክ እግዚአብሔር ነው

ጌታ ልክ ነው የሱስ ልክ ነው

በስራው ፃዲቅ ትክክለኛ እርሱ ብቻ ነው (፪x)

ጌታ ልክ ነህ የሱስ ልክ ነህ

በስራህ ፃዲቅ ትክክለኛ አንተ ብቻ ነህ (፪x)

ሁሉ ሲመቸው ነገር ሲሞላ

ህይወት ስትሆን ደግሞም በዝቅታ

ምናልፍበት መንገድ ሁሉም ለበጎ ነው

ተሳስቶ አይደለም እግዚአብሔር ልክ ነው

ጌታ ልክ ነው የሱስ ልክ ነው

በስራው ፃዲቅ ትክክለኛ እርሱ ብቻ ነው (፪x)

ጌታ ልክ ነህ የሱስ ልክ ነህ

በስራህ ፃዲቅ ትክክለኛ አንተ ብቻ ነህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ