Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ንፁህ ልብን

Netsuh Leben

2014 · ትራክ 5 · 3:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጠላቴን መውደድ እንድችል

ለክፉ መልካም እንዳደርግ

ብርሃኔ እንዲበራ

በቅንነት እንድኖር (፪x)

ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ ፍጠርልኝ እና

ባንተ የታየው በኔ እንዲታይ ጌታ

ያለኝን መስጠት እንድችል

ፍቅርህ በዝቶ እንዲገለጥ

እውነት በኔ እንድትታይ

ለሌሎች ምሳሌ እንድሆን (፪x)

ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ ፍጠርልኝ እና

ባንተ የታየው በኔ እንዲታይ የሱስ

ቅንነት ትግስትን ለብሼ ልገኝ ሁል ጊዜ

ፍቅር ይሁን መታወቂያዬ ጌታ አንተን መምሰሌ /4

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ