Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምክንያቱ

Mekneyatu

2014 · ትራክ 4 · 4:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባለፍኩበት በሄድኩበት በመንገዴ ሁሉ

ከነበርኩባቸው አስጨናቂ ቀኖቼ

ፀጋህ ምህረትህ እያገዘኝ

ዛሬን አደረሰኝ

ምክንያቱ ነህ አንተ ዛሬን ለመድረሴ

ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ (፪x)

ከማህፀን ገና ሳለሁ በስሜ የጠራኸኝ

ከልጅነቴ ጀምሮ መንገድ የመራኸኝ

ከጥፋት ጎዳና ጠበከኝ ዛሬን አሳየኸኝ

ምክንያቱ ነህ አንተ ዛሬን ለማየቴ

ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ (፪x)

ከኔ የሆነ ከቶ ምንም የለም

ሁሉ ባንተ ነው የሆነው

ከኔ የሆነ ከቶ ምንም የለም

ሁሉ ካንተ ነው የሆነው

ምክንያቱ ነህ አንተ ዛሬን ለመድረሴ

ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ (፪x)

ምክንያቱ ነህ አንተ በህይወት ለመኖሬ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ