Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተናግሮ አይረሳም

Tenagro Ayeresam

2014 · ትራክ 10 · 3:30 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሄር ያለው ሁሉ ይሆናል

አንድም ሳይቀር ይፈፀማል

የተናገረውን ቃሉን ያስባል

ሰው እኮ አይደለም እንዴት ይረሳል

ተናግሮ አይረሳም ተናግሮ አይረሳም

ከአፉ የወጣው በርግጥ ይፈፀማል (፪x)

ይሄ እንዴት ይሆን ከቶ አይባልም

በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለ ወይ

ላይጨርስ እርሱ አያስጀምርም

የእውነት አምላክ ነው ፈፅሞ አይዋሽም

ተናግሮ አይረሳም ተናግሮ አይረሳም

ከአፉ የወጣው በርግጥ ይፈፀማል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ