መኖሪያዬ
Menoriyayie
2014 · ትራክ 3 · 3:48 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ ነው
በክንዶቹ ጥላ አርፋለሁ
የሚያስፈራኝ ሁሉ ተወግዷል
ህይወቴን በሰላም ሞልቶታል (፪x)
አዝማች · Chorus
የለም እንደ ጌታ የለም
የለም እንደ ኢየሱስ የለም
አይኖርም ዘላለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰማይ በምድር የለም የሚመስለው
እግዚአብሔር እጅግ ልዩ ነው (፪x)
እንዲህ ነህ ተብሎ ማይገመተው
ከሰው ልጅ እጅግ የላቀ ከፍም ያለ ነው
አዝማች · Chorus
የለም እንደ ጌታ የለም
የለም እንደ ኢየሱስ የለም
አይኖርም ዘላለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሞተውን ነገር ህያው ነው የሚለው እግዚአብሔር ብቻ ነው
ያለቀውን ነገር ይሞላል የሚለው እግዚአብሔር ብቻ ነው (፪x)
እረኛውን አይቶ ንጉስ ነህ የሚለው እግዚአብሔር ብቻ ነው/2
አዝማች · Chorus
የለም እንደ ጌታ የለም
የለም እንደ ኢየሱስ የለም
አይኖርም ዘላለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ