Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አይቼሃለሁ

Ayechiehalehu

2014 · ትራክ 11 · 3:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያኔ ገና በለጋነት ኑሮ

ደርሰህ ባታወጣኝ ከጨለማው ጉዞ

እንዴት እሆን ነበረ ያኔ ለብቻዬ

ግን ሁሉን አለፍኩት ካንተ ጋራ ሆኜ

አይቼሃለሁ ከጎኔ ነበርክ

አይቼሃለው ስትረዳኝ

ከጎኔ ሆንህ ስታግዘኝ

ከፊቴ ሆነህ ስትመራኝ

ስወድቅ ቀድመህ ስታነሳኝ (፪x)

የቅርብ ምለው ካጠገቤ ርቆ

ቀኑ ጨሎብኝ ሁኔታውም ከብዶ

አንት ግን በሁሉ ብርታት ሆነኸኛል

እንባዬን አብሰህ እጆቼን ይዘሃል

አይቼሃለሁ ከሆኔ ነበርክ

አይቼሃለው ስትረዳኝ

ከጎኔ ሆንህ ስታግዘኝ

ከፊቴ ሆነህ ስትመራኝ

ስወድቅ ቀድመህ ስታነሳኝ (፪x)

አይቼሃለው አይቼሃለው አይቼሃለው ጌታ

ስወድቅ ስታነሳኝ ከፊት ስትመራኝ አይቼሃለው ጌታ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ