Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድነናል

Denenal

2014 · ትራክ 9 · 4:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በበደል በሀጥያት ሙታን የነበርነው

ከመንግስቱ ጠፍተን ተጨንቀን ላለነው

ከኢየሱስ ጋር ህይወትን አገኘን

በርግጥ ሞተን ነበር በፀጋው አዳነን (፪x)

ድነናል ድነናል በፀጋው ድነናል /3

በጠላት እስራት በጨለማ ሆነን

መሄጃው ጠፍቶብን ተስፋ ቆርጠን ሳለን

አርነት ሊያወጣን ስለኛ ቆሰለ

ሞታችንን ሞቶ በህይወት አኖረን (፪x)

ድነናል ድነናል በፀጋው ድነናል /3

በርግጥ ሞተን ነበር በጌታ ድነናል

የዘላለም ህይወት በነፃ አግኝተናል

ክሳችንን ከኛ ከኛ ላይ ወስዶታል

ማይጠፋውን ህይወት በነፃ አግኝተናል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ