Azeb Hailu/Ashenafi Negn/Mulu Sewenet
2004 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሙሉ መስዋዕት እንከን የሌለው ኦሆ
ለአማልክት አምላክ ይዣለሁ ይኸው አሃ
የማያነክስ ወይ ያልታወረ ኦሆ
ለጌቶች ጌታ ለተከበረ አሃ
በፊቱ የተወደደ
በፊቱ ከቶ ያልተናቀ
ሊያሸተው በአምላኬ ዘንድ
ዘወትር የተናፈቀ
ቅዱሱም ሕያው መስዋዕት
እራሴ ነው ሰውነቴ
ላፍስሰውና ልሰዋው
ደስ ይበለው መድኃኒቴ
አዝማች · Chorus
ለአምላኬ
ምሥጋናዬን እሰዋለሁ
ለንጉሡ
ስዕለቴን እከፍላለሁ
ይህ ለእኔ
ሥራዬ ነው ልማዴ
በወቅቱ
ክብርን መስጠት ለውዴ
ይሄ ነው ልማዴ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሙሉ ለሙሉ ጭሶ የሚቃጠል ኦሆ
በዙፋኑ ላይ እሰይ የሚያስብል አሃ
ያለቁጠባ ያለ ስስት ኦሆ
በማደሪያው ላይ ይሽተትለት አሃ
ከነፍሴ ከፍፁም ደስታ
የነፍሴ ነው ከፍቃዴ
በጠዋትና በማታ
የምሰዋለት ለውዴ
የተመረጠውን መስዋዕት
ከስቡ እና ከበኩሩ
አምላኬን ደስ ካሰኘው
ይኸው ለዝናው ለክብሩ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለጌታ
ቁጥር 4 · Verse 4
ምሥጋናዬን እሰዋለሁ
ለልዑሉ
ስዕለቴን እከፍላለሁ
ይህ ለእኔ
ሥራዬ ነው ልማዴ
በወቅቱ
ክብርን መስጠት ለውዴ
ይሄ ነው ልማዴ (፫x)
የደመናትን ድንበር የሚጥስ ኦሆ
ወደ ማደሪያው የሚገሰግስ አሃ
የተወደደው ውድ ምሥጋና ኦሆ
የተገባው አምላክ ነውና አሃ
በምድር እስካለሁባት እስከ ኖርኩባት ዘመኔ
የሚገባውን በሙሉ አላጓድልም ከእኔ
በማንኛውም ሁኔታ በማንኛውም ሰዓት
እርሱ ይቀበለኝ እንጂ አልሰለችም መሰዋት
አዝማች · Chorus
ለአምላኬ
ምሥጋናዬን እሰዋለሁ
ለንጉሡ
ስዕለቴን እከፍላለሁ
ይህ ለእኔ
ሥራዬ ነው ልማዴ
በወቅቱ
ክብርን መስጠት ለውዴ
ይሄ ነው ልማዴ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ