አሸናፊ ነኝ
Ashenafi Negn
2004 · ትራክ 1 · 6:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ ጀግና ወንድ/ሰው እንደ እልፍ ገዳይ
እንጐራደዳለሁ/ፎክርበታለሁ በጠላቴ ላይ
ተረታው ሳይል እጁን ዘርግቶ
ማጥቃት መዋጋትን አልተውም ከቶ (፪x)
ተወርውሮ ከቶ የማይስተው
የጌታዬ የኢየሱስ ሥም ነው
ደጋግሜ እርሱን ጠራዋለሁ
በጠላቴ ላይ ከፍ እላለሁ
ሲቀረቀር በግንባሩ ላይ
በእጄ ያለው የያዝኩት ድንጋይ
ላዩ ቆሜ አንገቱን ቆርጥና
አውጃለሁ የጌታዬን ዝና
አዝማች · Chorus
አሸናፊ ነኝ የጌታ/የኢየሱስ ሆኜ
አፍሬ አላውቅም እርሱን ታምኜ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔም እንደ ዳዊት እንደ እግዚአብሔር ሰው
በሕዝቤ ጠላት ላይ ሥምህን ላንሳው
በሰልፉ ሜዳ ላይ ወደ መሃል ልግባ
ጠላትን ዘርሬ ላፍስስ የደስታ እንባ
እኔ እያየሁ ጐልያድ በእስራኤል ላይ አይፎክርም
እኔ እያለሁ ጠላት በሕዝቤ/በምድሬ ላይ አይዘብትም (፪x)
የአንበሳን ደቦል የሚገነጥል
ግዙፉን ሠራዊት ሰባብሮ የሚጥል
የአምላኬ ክብሩ ነው ከእኔ ጋራ
ከቶ እንደምን ልስጋ እንዴትስ ልፍራ (፪x)
ፍልስጤሞች ያገኙኝ መስሏቸው
በመንደሩ ሞላ ዕልልታቸው
በጠንካራዉ ገመድ አስረውኛለው
በእነሱ ቤት ማን ያስጥለኛል
ወረደብኝ መንፈሱ የጌታ
እስራቴም ላላ ተፈታታ
በእጄ ገቡ ጠፉ ጠላቶቼ
ገመድኳቸው መጥቼ ፈትቼ
አዝማች · Chorus
አሸናፊ ነኝ የጌታ/የኢየሱስ ሆኜ
አፍሬ አላውቅም እርሱን ታምኜ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አሞት ይሆናል ወይ መንገድ ሄዶ
አንቀላፍቶም ይሁን ይህ ከንቱ ባዶ
በአሕዛብ አምላክ እሳለቃለሁ
በማንነቱም ላይ እዘብታለሁ (፪x)
አምላክ ሳይሆን አምላክ ነኝ ባዩን
መዘዝኩበት ስለታም ሰይፌን
ነብያቱን በሙሉ አረድኳቸው
እስቲ ያድን ይምጣ አምላካቸው
የሚመልስ በእሳት ተገልጦ
የአሕዛብን አምላክ አስደንግጦ
የእኔ ጌታ ሥሙም እግዚአብሔር
ከፍ ብሎ ተከብሮ የሚኖር
አዝማች · Chorus
አሸናፊ ነኝ የጌታ/የኢየሱስ ሆኜ
አፍሬ አላውቅም እርሱን ታምኜ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ኤልያስ
በምድር ኢትዮጵያ ላይ ሥምህ እንዲነግስ
ከበአል ነቢያት እወራረዳለሁ
ክብርህን ስትገልጥ እረታቸዋለሁ
እኔ እያየሁ በአል አምላክ ተብሎ አይመለክም
እኔ እያለሁ የጌታዬ/የኢየሱስ ክብር አይሸፈንም (፪x)
አንተ እያለህ እውነት እንጂ ውሸት አይሰበክም
አንተ እያለህ ወንጌል እንጂ ክደት አይነገርም
አንቺ እያለሽ እውነት እንጂ ውሸት አይሰበክም
አንቺ እያለሽ ወንጌል እንጂ ክደት አይነገርም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ