ሙሽራዪቱ ሆይ ተነሺ
Musherayitu Hoy Teneshi
2004 · ትራክ 12 · 4:38 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የልዑሉ አምላክ ማደሪያ
አካሉ የሆንሽ የእርሱ መኖሪያ
አንች ቤተክርስቲን ተነሺ
የሰጠሽን ተስፋ አትርሺ
ሁኝ እንጂ ልክ እንደ ሙሽራ
ልትቆሚ እኮ ነው በተራራ
የሰርግሽ ቀን በጣም ቅርብ ነው
ሙሽራሽ ደጂ እያንኳኳ ነው
ዘምሪለት እንጂ በዕልልታ
የምን በራድ ትኩስ ለብታ
ድመቂ ንሺ ተቀደሽ
ሙሽራይቱ ሆይ ተነሽ
መቅረዝሽ በዘይት ይሞላ
በር እንዳይዘጋብሽ ኋላ
ቀን ሳላ ዛሬ ተዘጋጂ
በፍጻሜው እንዳትጐጂ
ረሻሽ ወይ ጌታሽ መመለሱን
ጠብቂኝ እመጣለህ ማለቱን
መዘናጋቱ ምነው በዛ
ጣል እረግሽው ልክ እንደዋዛ
የወደፊቱ ክብር ተስፋ
ተጋረደ ከዓይንሽ ስር ጠፋ
አዝማች · Chorus
ጊዜው ደርሷል እባክሽን ንቂ
ቤተክርስቲያን ተጠንቀቂ
ሊያደርግሽ ፍሬ አልባ ገለባ
የዓለም ኮተት ሰርጐ ገባ
ተኝተሽ ጠላት ዘሩን ዘራ
ምድርሽ እንክርዳድን አፈራ
በበጉ ደም ፈጥነሽ ታጠቢ
አስታውሺ ተስፋሽን አስቢ
የሰርጉ ቀን በጣም ተቃርቧል
ሙሽራሽ ወደ አንቺ ይመጣል
አሜን ማራናታ ቶሎ ና
የምትይበት ጊዜው ነውና
ይሰማ ድምፅሽ ያስተጋባ
ወደ ልዑል ማደሪያ ይግባ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከእንግዲህ በምድር ምን ቀረሺ
ናፍቂ ወደሰማይ ገስግሺ
ይልቃል በዚያ ያለው ደስታ
ማሰማት ዝማሬና ዕልልታ
በዚያ እኮ ርሃብ ጥማት የለም
ደዌ ህመም አይታወቅም
እንባ ከዓይኖችሽ ይታበሳል
በጉ የአንች እረኛ ይሆናል
የበጉ መሽራ አንቺ ሆይ
ይህ ክበር አልናፈቀሽም ወይ
ይመጣል ወዳጅሽ ወደ አንቺ
ተነሽ ቁሚ ተዘጋጂ
አዝማች · Chorus
ማራናታ ፣ ማራናታ
አሜን ጌታ ሆይ ተሎ ና
አሜን ኢየሱስ ተሎ ና
አሜን ጌታ ሆይ ተሎ ና
አሜን ኢየሱስ ተሎ ና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ