Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ካህኔ

Kahenie

2004 · ትራክ 10 · 5:18 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ

በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ

ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል

ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል

ካህኔ እንደመልከፄዴቅ : ካህኔ ለዘላለም ሹም ነህ

ካህኔ ለእኔም ሕይወት መዳን : ካህኔ ምክንያቱ አንተ ነህ

ካህኔ በማይጠፋው ክህነት : ካህኔ በማይሽረው ሞት

ካህኔ የምትማልድልኝ : ካህኔ ቆመህ በአብ ፊት

ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ

ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር

በማለዳ በቀትር በማታ

አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (፪x)

ካህኔ በአብ ቀኝ ያለሀው : ካህኔ የነፍሴ ጠበቃ

ካህኔ መከራዬ እንዲቆም : ካህኔ ሀዘኔ እንዲያበቃ

ካህኔ የጥልን ግድግዳ : ካህኔ በሞት አፈረስህ

ካህኔ ለበደሌ መስዋዕት : ካህኔ ደምህን አፈሰስህ

በሞት ያልተሻረ በሞት ያልተገታ

በሰማይም ቀጥሏል ክህነቱ የጌታ

ሌሎቹ እንዳይኖሩ ሞት ከልክሏቸዋል

ከነአሮን ክህነት የኢየሱስ ይበልጣል

የካህናት አለቃ የበጎች እረኛ

የእውነተኛዋ ድንኳን : መካከለኛ

በኔ ፈንታ የሞተ የሆነልኝ ቤዛ

ነፍሴ በጣም ረክታለች ለእርሱ ስትገዛ

መድህኔ የመቀበርያዬን : መድህኔ ጉድጓድ የደፈንከው

መድህኔ የሕይወቴን ጨለማ : መድህኔ ገለል ያደረከው

መድህኔ በሞትና በእኔ : መድህኔ መካከል ገብተህ

መድህኔ ሕያው አደረከኝ : መድህኔ አንተ ተችሎህ

ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ

ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር

በማለዳ በቀትር በማታ

አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (፪x)

መድህኔ ዛሬስ ብርሃን ነው : መድህኔ ቀን ሆኖ ለነፍሴ

መድህኔ ባንተ ተሰበረ : መድህኔ ለቅሶና ትካዜ

መድህኔ ፍጻሜዬ እንዲያምር : መድህኔ የመጨረሻዬ

መድህኔ አንተን መጠጋቴ : መድህኔ ልክ ነው ምርጫዬ

ምን እላለሁ ከምስጋና ሌላ

ምን እሰጣለሁ ከማመስገን በቀር

በማለዳ በቀትር በማታ

አምላኬ ሆይ ልበል ክበር ክበር (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ