Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እያስገረመኝ

Eyasgeremegn

2004 · ትራክ 11 · 5:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ውለታውን ተናግሮ ያበቃ

እግዚአብሔርን አክብሮ የረካ

ማነው እርሱ ምሥጋና ያለቀበት

ያልተረዳ የዛሬውን ምህረት

ከትናንቱ በላይ እንደሆነ

በብዙ እጥፍ : ብዝቶ እንደገነነ

የዛሬውን ቸርነት/ደግነት የረሳ

ለማመሥገን በፍጥነት ይነሳ (፪x)

እኔስ ከትናንቱ የዛሬው ባሰበኝ

ካለፉት ዓመታት የሆነው ላቀብኝ

ፍቅር ደግነቱ ምህረቱ ገነነ

ከማስበው በላይ መልካም የሆነ

እያስገረመኝ እያስደነቀኝ ሁሌ እያሳቀኝ

አፌን በምስጋና: ምላሴን በዕልልታ እየሞላብኝ

ነፍሴን የሚያረካ ክብሩን እያሳየኝ

እንዴት ዝም እላለሁ

ዘወትር በየለቱ ሁልጊዜ ጌታዬ አመሠግናለሁ (፭x)

ተናግሬ ሳልጨርስ ተዓምሩን

ይገልጠዋል በድጋሚ: ክብሩን

በላይ በላይ እየጨማመረ

እያበዛ ደግሞ እያከበረ

በዘመናትና በዓመታቱ

ሳያጓድል ሳይሰስት ንብረቱን

ያስጉዘኛል/ያስኬደኛል በድል ሰረገላ

ምን ልበለው ከተመሥገነ ሌላ (፪x)

ምስጋናዬ የበዛበት ምክንያቴ ብዙ ብዙ ነው

የተጙዝኩበት ጎዳና ያ ዘመን ምስክሬ ነው

ካንደኛው የህይወት ምዕራፍ ወደሌላው ስሸጋገር

ብርሀኑን እያበራ የመራኝ አምላኬ ይክበር (፪x)

ማዳኑን ስላየሁ አመሠግናለሁ (፫x)

ፍቅሩን ቀምሼ እንዴት ዝም እላለሁ (፫x)

ቀኖቹ ቢያወሩ ቢመሰክሩት (፫x)

አቤት ለእኔ ያደረገው ድንቅ ተዓምራት (፫x)

ሥሙን እባርከዋለሁ (፫x)

ሥሙን እቀድሰዋለሁ (፫x)

ነፍሴና ሥጋዬ ምሥጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ

አጥንቶቼም ጭምር ምሥጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ

የሰራላችሁን የማዳኑ ሥራ አስቡ (፪x)

አልበቃኝም አመሥግኜው (፪x) አልበቃኝም

እኔ አልረካሁም አመሥግኜው (፪x) አልረካሁም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ