ክበር እላለሁ
Keber Elalehu
2004 · ትራክ 14 · 5:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ
ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ
እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ
ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ
አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ
እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ
በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ
የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ
ክበር እላለሁ (፫x) ስትከብር እጠግባለሁ
ንገሥ እላለሁ (፫x) ስትነግሥ እረካለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
እየደጋገሙ ሥሙን ለሚያነሱ
የሚወዱትን ነው የሚያሞጋግሱ
እኔም በአንተ ፍቅር ስለተያዝኩኝ
ነግቶ እስከሚመሽ እጣራለሁኝ (፪x)
ጌታ እላለሁኝ
አምላኬ እላለሁኝ
ወዳጄ እላለሁኝ
ረዳቴ እላለሁኝ
አዝማች · Chorus
ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ
ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ
እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ
ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ
አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ
እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ
በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ
የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ
ክበር እላለሁ (፫x) ስትከብር እጠግባለሁ
ንገሥ እላለሁ (፫x) ስትነግሥ እረካለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳይሰላቹና ፍፁም ሳይታክቱ
ክብርን ይሰጡሃል በላይ መላዕክቱ
እኔም ባለሁበት ድንኳን በጓዳዬ
ለምወድህ ጌታ ይኸው ምሥጋናዬ (፪x)
ይብዛልህ ወብ አምልኮዬ
ይብዛልህ ወብ ዝማርዬ
ይብዛልህ ውብ ዕልልታዬ
ይብዛልህ ውብ ምሥጋናዬ
አዝማች · Chorus
ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ
ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ
እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ
ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ
አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ
እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ
በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ
የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ
ክበር እላለሁ (፫x) ስትከብር እጠግባለሁ
ንገሥ እላለሁ (፫x) ስትነግሥ እረካለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሥምህ በከንፈሬ ላይ እጅግ ጣፍጦኛል
ባስታወስኩት ቁጥር ደስ ደስ ይለኛል
አንዳንዴም ስደክም አቅም ሲከዳኝ
አምላኬን ስጠራው እበረታለሁኝ (፪x)
ጉልበቴ እላለሁኝ
ብርታቴ እላለሁኝ
ድጋፌ እላለሁኝ
ምርኩዜ እላለሁኝ
አዝማች · Chorus
ነግቶ እስከሚመሽ መሽቶም እስኪነጋ
ስላንተ ብጫወት ስላንተ ባዎጋ
እኔ አይሰለቸኝም አልታክትም ከቶ
ምላሴም አይደክም ፍቅርህን አውግቶ
አመሰግናለሁ ደግሜ ደግሜ
እጅግ በገነነው ዙፋንህ ሥር ቆሜ
በተመረጠ ቃል በሚጣፍጥ ዜማ
የከንፈሬን ፍሬ መዝሙሬን ላሰማ
ክበር እላለሁ (፫x) ስትከብር እጠግባለሁ
ንገሥ እላለሁ (፫x) ስትነግሥ እረካለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ