Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እልፍ ወደ ማዶ

Elef Wede Mado

2004 · ትራክ 3 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ

እልፍ ወደ ማዶ

አረገኝ ማዳኑን ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ

ሊያሳየኝ አቅዶ

ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ

ፈቀቅ ወደ ጥልቁ

አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ

ሁሉ እንዲደነቁ

ከልምምድ ውጪ ከተዘወተረው

አዲስ ነገር መስራት ልማዱ የሆነው

በውኃ ላይ እንድሄድ እንድቆም አዘዘኝ

ቃል ላከልኝና አትፍሪ ነይ አለኝ

ውኃ ላይ በታንኳ ሁሌ ከመንሳፈፍ

ኢሄም አለ ብሎ አደረገኝ እልፍ

ከታንኳ ያልወረዱ ቢሉም ምትሃት ነው

ለካስ የእኔ ጌታ ውኃም መንገዱ ነው

እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ

እልፍ ወደ ማዶ

አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ

ሊያሳየኝ አቅዶ

ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ

ፈቀቅ ወደ ጥልቁ

አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ

ሁሉ እንዲደነቁ

እንሂድ ወዲያማዶ እንሂድ እንሻገር

ሥሙም ጌርጌስኖን ወደሚባል አገር

ለረጅም ዘመናት ብዙ የተቸገረ

በመቃብር ስፍራ አለና የታሰረ

እልፍ እንበልና የታሰረ ይፈታል

ብሎ ሲያሻግረን ይሄ ቸሩ ጌታ

በስፍራው ስንደርስ ይህ ሰው ተፈወሰ

ጌታም ተገናኘው ልቡም ተመለሰ

እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ

እልፍ ወደ ማዶ

አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ

ሊያሳየኝ አቅዶ

ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ

ፈቀቅ ወደ ጥልቁ

አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ

ሁሉ እንዲደነቁ

ሌሊቱን በሙሉ ስደክም ፍለጋ

መረቤም አንድ ዓሣ ሳይዝልኝ ነጋ

የጌታን ቃል ይዤ ስጥል ወደ ጥልቁ

ታንኳዬን ዓሣዎች ሞልተው አስጨነቁ

መሄድ እንደቃሉ ፈቀቅ ማለት

በውስጡ አለና ብዙ በረከት

ገፍቶ አስጠግቶኝ አድርጐኝ እልፍ

በመንፈሱ ሙላት ሆነ መንሳፈፍ

እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ

እልፍ ወደ ማዶ

አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ

ሊያሳየኝ አቅዶ

ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ

ፈቀቅ ወደ ጥልቁ

አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ

ሁሉ እንዲደነቁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ