ዛሬም ይወደኛል
Zariem Yewedegnal
2004 · ትራክ 7 · 6:24 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አሃ አሃሃ ያኔ እንደወደደኝ
አሃ አሃሃ ዛሬም ይወደኛል
አሃ አሃሃ የእኔ ጌታ ፍቅሩ
አሃ አሃሃ መች ቀንሶ ያውቃል
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተለዋወጠም
አሃሃ ምህረቱ ዛሬም አልጐደለም
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተቀያየረም
አሃሃ ቸርነቱ ዛሬም አልጐደለም
ቁጥር 1 · Verse 1
ያኔ በመስቀል ላይ ሆኖ ኤሎሂ ያለላት
ከሲዖል እንድትድን ወዶ የተሟገተላት
ሞቶ እስከሚቀበር ድረስ የወደዳት ነፍሴ
ትገዛለታለች ዛሬም እያለች ንጉሤ
ወዶኛልና አዳነኝ
እያለች ቅኔ ስትቀኝ
ላልተለወጠው ማንነትህ
ምሥጋናም አላት ለምህረትህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አሃ አሃሃ ያኔ እንደወደደኝ
አሃ አሃሃ ዛሬም ይወደኛል
አሃ አሃሃ የእኔ ጌታ ፍቅሩ
አሃ አሃሃ መች ቀንሶ ያውቃል
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተለዋወጠም
አሃሃ ምህረቱ ዛሬም አልጐደለም
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተቀያየረም
አሃሃ ቸርነቱ ዛሬም አልጐደለም
ቁጥር 2 · Verse 2
በሕይወቴ ውጣ ውረድ ባልፍም በመከራ
እርሱ ፈፅሞ አልተወኝም አለ ከእኔ ጋራ
ዓመት ዘመን ቢለዋወጥ ቀንም በቀን ላይ
እንከን አላየሁበትም ውዴም ፍቅሩ ላይ
በምህረቱ ባለጠጋ
ሆኖ አየሁ ወደ እርሱ ስጠጋ
አይጨምርም አይቀንስ ፍቅሩ
እርሱ ያው ነው በዘመኑ (፪x)
አዝማች · Chorus
አሃ አሃሃ ያኔ እንደወደደኝ
አሃ አሃሃ ዛሬም ይወደኛል
አሃ አሃሃ የእኔ ጌታ ፍቅሩ
አሃ አሃሃ መች ቀንሶ ያውቃል
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተለዋወጠም
አሃሃ ምህረቱ ዛሬም አልጐደለም
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተቀያየረም
አሃሃ ቸርነቱ ዛሬም አልጐደለም
ቁጥር 3 · Verse 3
የመልካምነቱን ብዛት ማን ቆጥሮ ይዘልቃል
ከሰማያት ከፍ ያለ ነው ከሲዖል ይጠልቃል
ማነው ወዳጅ እንደ ጌታ ከቶ በዓለም ላይ
እንኳን ከሰው ከዚች በምድር የለም በሰማይ
ወዶኛልና አዳነኝ
እያልኩኝ ቅኔው ስቀኝ
ላልተለወጠው ማንነትህ
ምሥጋናም አለኝ ለምህረትህ (፪x)
አዝማች · Chorus
አሃ አሃሃ ያኔ እንደወደደኝ
አሃ አሃሃ ዛሬም ይወደኛል
አሃ አሃሃ የእኔ ጌታ ፍቅሩ
አሃ አሃሃ መች ቀንሶ ያውቃል
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተለዋወጠም
አሃሃ ምህረቱ ዛሬም አልጐደለም
አሃሃ እርሱ ያው ነው አልተቀያየረም
አሃሃ ቸርነቱ ዛሬም አልጐደለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ