ሥሙ ሞገሳም ነው
Semu Mogesam New
2004 · ትራክ 9 · 4:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንኳን ማንነቱ ሥሙ ሞገሳም ነው
ወዶ አይደለም ፍጥረት ሰዎች የሚርበደበደው
ከወዲህ ተጠርቶ ከማዶ ይሰራል
ድንገት ደርሶ የጠላትን ምሽግ ያሸብራል
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ የሚለው ሥም ብርቱ ጉልበት አለበት
ቁጥር 2 · Verse 2
አይቻለሁ ጠላቶቼ ሲመታ ሲያንቀጠቅጥ (፪x)
እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው
በሰማይም ኢየሱስ ነው
በምድርም ኢየሱስ ነው
ከምድር በታች ኢየሱስ ነው
በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (፪x)
የበሽታ ብርታት የደዌ ጉልበት
አይፈልግም የጌታ ሥም እንዲጠራበት
በሥጋ ለባሽ ላይ የሚበረታው
ያውቃል ከተጠራ ሥሙ እንደሚነቅለው
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ የሚለው ሥም ታላቅ ጉልበት አለበት
ቁጥር 3 · Verse 3
አይቻለሁ ለህመሜ ሲሆን መድኃኒት (፪x)
እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው
በሰማይም ኢየሱስ ነው
በምድርም ኢየሱስ ነው
ከምድር በታች ኢየሱስ ነው
በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (፪x)
የመከራን ጭጋግ የሚችል መግፈፍ
በእውነተኛው በረከት የሚያትረፈርፍ
የባዶ ሸለቆ የመሙላት ሚስጥር
ሲጠራ ነው የኢየሱስ ሥም በታላቅ ክብር
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ የሚለው ሥም ደግነትም አለበት
ቁጥር 4 · Verse 4
አይቻለሁ በጓዳዬ ሲሆንልኝ በረከት (፪x)
እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያረገው
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምም የተሰጠው
በሰማይም ኢየሱስ ነው
በምድርም ኢየሱስ ነው
ከምድር በታች ኢየሱስ ነው
በሁሉ ላይ ኢየሱስ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ