ሚስጥርን የሚገልጽ
Misteren Yemigelts
2004 · ትራክ 8 · 4:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሚስጥርን የሚገልጥ በሰማይ ውስጥ አለ
ዙፋኑ በብዙ ክብር የተከለለ
ከሰው ልብ የጠፋን ህልም ከነፍቺው
የሚያቀብል አምላክ እግዚአብሔር ነው (፪x)
ዙፋኑ በሰማይ ርቆ ከፍ ቢልም
በዓይኖቹ ከማየት ፍፁም አይታክትም
የተሰወረውን በታች በሸለቆ
እርሱ ወደ ብርሃን ይገልጠዋል አውቆ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማነው ከፊቱ የሚሰወር
ማነው ከእርሱ የሚደበቅ
ማነው ወጥቶ የሚገባ
ማነው አምላኬ ሳያውቅ
ያያል ያያል ሁሉን ነገር ያያል
ያውቃል ያውቃል አስተውሎ ያውቃል
ዝም ቢል ቢታገስ ለፍርድ ባይቸኩል
የተወህ የረሳህ ያላየህ አይምሰልህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የቀድሞውን ዘመን ወይንም የአሁኑ
ገና የሚመጣውን የወደፊቱን
የፍጥረትን ሩጫ ሙሉ እንቅስቃሴ
እርሱ ብቻ ያውቃል አምላኬ ንጉሤ (፪x)
ነገር ሁሉ ፊቱ ዕርቃኑን ይቆማል
ማን ከእርሱ ሚስጥሩን ደብቆ ያኖራል
የሰማይ የምድሩን ሁሉንም አዋቂ
ከስውርም ወጥመድ አዳኝ ነው ነጣቂ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማነው ከፊቱ የሚሰወር
ማነው ከእርሱ የሚደበቅ
ማነው ወጥቶ የሚገባ
ማነው አምላኬ ሳያውቅ
ያያል ያያል ሁሉን ነገር ያያል
ያውቃል ያውቃል አስተውሎ ያውቃል
ዝም ቢል ቢታገስ ለፍርድ ባይቸኩል
የተወህ የረሳህ ያላየህ አይምሰልህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ