በዓለም ጨለማ
Bealem Chelema
2010 · ትራክ 1 · 3:04 · አማርኛ
በዓለም ጨለማ እውር ሆኜ ሳለሁ
አንድ ቀን ኢየሱስ ዓይኔን ከፍቶት አየሁ (፫x)
አንድ ቀን ኢየሱስ ዓይኔን ከፍቶት አየሁ
ብርሃኔ ተገፎ በዓለም ስደናቀፍ
ዓይኔን ከፈተልኝ ኢየሱስ ሥሙ ይክበር (፫x)
ዓይኔን ከፈተልኝ ኢየሱስ ሳሙ ይክበር
ከጉዳት የሚያድን መሪ እንኳን ሳይንረኝ
አንድ ኢየሱስ ብቻ እረዳት ሆነልኝ (፫x)
አንድ ኢየሱስ ብቻ እረዳት ሆነልኝ
ከጥንት ከበፊቱ እውር እንደነበርኩ
አሁን ግን እንደማይ ይህንን አውቃለሁ ሥሙ ይክበር (፪x)
አሁን ግን እንደማይ ይህንን አውቃለሁ
ከሸንጐም ብወጣ በማንም ብጠላ
ጌታን አመልካለሁ የሕይወቴን ከለላ (፫x)
ጌታን አመልካለሁ የሕይወቴን ከለላ
ጠቃሚና ጐጂውን የማላውቅ ለይቼ
ብርሃኔ ተገልጦ ደስ አለኝ አይቼ (፫x)
ብርሃኔ ተገልጦ ደስ አለኝ አይቼ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ