Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የተሰዋህ

Yetesewah

2010 · ትራክ 6 · 5:06 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የተሰዋህ የእግዚአብሔር በግ

የሞትክልኝ አምላኬ ሆይ

ጭንቀት ጣርህ ለነፍሴ ይታይ (፪x)

ሃዘን ውጦኝ ሳለሁ ተጨንቄ

በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ወድቄ

ሳላስበው ድንገት ኢየሱስ ጠርቶኝ

የሕይወትን ውኃ አፈሰሰልኝ

የተሰዋህ የእግዚአብሔር በግ

የሞትክልኝ አምላኬ ሆይ

ጭንቀት ጣርህ ለነፍሴ ይታይ (፪x)

የኀጢአት ሸክም እጅግ ጀብዶብኝ

ምንም አጥቼ የሚረዳኝ

ኢየሱሴ ድንገት ደርሶልኝ

ከድካሜ ሁሉ አሳረፈኝ

የተሰዋህ የእግዚአብሔር በግ

የሞትክልኝ አምላኬ ሆይ

ጭንቀት ጣርህ ለነፍሴ ይታይ (፪x)

በሰይጣን ሰንሰለት ታስሬ

ወደገሃነም እሳት ሳመራ

ኢየሱሴ ለእኔ ዋስ ሆኖ

አወጣኝ ከዚያ መከራ

የተሰዋህ የእግዚአብሔር በግ

የሞትክልኝ አምላኬ ሆይ

ጭንቀት ጣርህ ለነፍሴ ይታይ (፪x)

ተስፋ አልነበረኝም ከቶ

ከሲኦል ውስጥም ለመውጣቴ

በመስቀል ለእኔ ሞቶ አዳነኝ

ያየዋሁ ቸሩ አባቴ

የተሰዋህ የእግዚአብሔር በግ

የሞትክልኝ አምላኬ ሆይ

ጭንቀት ጣርህ ለነፍሴ ይታይ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ