Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እርስ በራሳችሁ

Ers Berasachehu

2010 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እርስ በእርሳችሁ በአንድ ሃሳብ ተስማሙ

የትዕቢትን ነገር አታስቡ (፬x)

ግቅራቹህ ያለግብዝነት ይሁን

ክፉውን ነገር ተጸየፉ

ከበጐ ነገር ጋር ተባበሩ

በወንድማማች መዋደድ ተዋደዱ

እርስ በእርሳችሁ በአንድ ሃሳብ ተስማሙ

የትዕቢትን ነገር አታስቡ (፪x)

እርስ በእርሳቹህ ተከባበሩ

ለስራ ከመትጋት አትለግሙ

በመንፈስ ግምት እንኳን ጥሩ ሁኑ

ደግሞም ለጌታ ተገዙ

እርስ በእርሳችሁ በአንድ ሃሳብ ተስማሙ

የትዕቢትን ነገር አታስቡ (፪x)

በተስፋም እጅግ ደስ ይበላቹህ

በመከራቹህ ሁሉ ታገሱ

በጸሎትም ሁሉ ደግሞ ጽኑ

ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ

እርስ በእርሳችሁ በአንድ ሃሳብ ተስማሙ

የትዕቢትን ነገር አታስቡ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ